The Mystery of Human Life (አማርኛ) | Words of Truth and Life

The Mystery of Human Life (አማርኛ)

This post is also available in: እንግሊዝኛ ዐረብኛ ፈረንሳይኛ ዕብራይስጥ ሩሲያዊ ጓደኛ

mohl-mysteryofhumanlife_am
“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር”

በዚህ ዓለም ለምን እንደምትኖርና የሕይወትህ ዓላማ ምን እንደሆነ አስበህ ታውቅ ይሆን? ይህንን ምስጢር የሚፈቱ ስድስት ቁልፎች አሉ።

1. የእግዚአብሔር እቅድGod-spirit_am
እግዚአብሔር ራሱን በሰው በኩል መግለጥ ይፈልጋል (ሮሜ 8፥29)። ለዚህም ዓላማ ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ (ዘፍ. 1፥26)። ልክ ጓንት እጅን በውስጡ አስገብቶ ለመያዝ በእጅ መልክ እንደተሰራ እንዲሁ ሰው ደግሞ እግዚአብሔርን በውስጡ ለመያዝ በእግዚአብሔር መልክ የተሰራ ነው። እንደይዘቱ እግዚአብሔርን በመቀበል፣ ሰው እግዚአብሔርን መግለጥ ይቻለዋል (2ቆሮ. 4፥7)።

2. ሰው
እቅዱን ለማሳካት እግዚአብሔር ሰውን እንደ ዕቃ አድርጎ ሰራው (ሮሜ 9፥21-24) ይህ ዕቃ ሦስት ክፍሎች አሉት፦ ሥጋ፣ ነፍስ፣ እና መንፈስ (1ተሰ. 5፥23)። ሥጋ የቁሳዊውን ዓለም ነገሮች ለመንካትና ለመቀበል ያገለግላል። ነፍስ ማለትም አእምሮአዊው ክፍል የስነልቦናዊውን ዓለም ነገሮች ለመንካትና ለመቀበል ያገለግላል። እጅግ ውስጠኛው የሆነው የሰው ክፍል ማለትም የሰው መንፈስ ደግሞ የተሰራው እግዚአብሔርን ለመንካትና ለመቀበል ነው (ዮሐ. 4፥24)። ሰው የተፈጠረው በሆዱ ምግብ ለማሳደር ወይም በአእምሮው እውቀት ለመያዝ ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን በመንፈሱ ለማሳደር ነው (ኤፌ. 5፥18)።

3. የሰው ውድቀት
ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን እንደ ሕይወት ወደ መንፈሱ ውስጥ ከመቀበሉ በፊት ኃጢአት ወደ ውስጡ ገባ (ሮሜ 5፥12)። ኃጢአት መንፈሱን ሙት አደረገው (ኤፌ. 2፥1)። በአእምሮው ደግሞ የእግዚአብሔር ጠላት አደረገው (ቆላ. 1፥21)። እንዲሁም አካሉን ወደ ኃጢአተኛ ሥጋነት ለወጠው (ዘፍ. 6፥3፤ ሮሜ 6፥12)። ስለዚህ ኃጢአት ሦስቱንም የሰው ክፍሎች በማበላሸት ሰውን ከእግዚአብሔር አቆራረጠው። በዚህ ሁኔታ ሰው እግዚአብሔርን ወደ ውስጡ መቀበል አይችልም።

4. ለእግዚአብሔር ማደል የክርስቶስ ቤዛነት
Process_am
ይሁን እንጂ፣ የሰው ውድቀት እግዚአብሔርን የመጀመሪያ እቅዱን ከመፈፀም አልከለከለውም። እቅዱን ለመፈፀም፣ እግዚአብሔር መጀመሪያ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚባል ሰው ሆነ (ዮሐ. 1፥1፣ 14)። ከዚያም ክርስቶስ ሰውን ሊቤዥ በመስቀል ላይ ሞተ (ኤፌ. 1፥7)፤ ይህም የሰውን ኃጢአት ለማስወገድ እና ሰውን ወደ እግዚአብሔር መልሶ ለማምጣት ነው (ዮሐ. 1፥29፤ ኤፌ. 2፥13)። በመጨረሻም፣ ፍለጋ የሌለው ባለጠጋ ሕይወቱን ወደ ሰው መንፈስ ውስጥ ማደል እንዲችል፣ በትንሳኤ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ሆነ (1ቆሮ. 15፥45፤ ዮሐ. 20፥22፤ 3፥6)።

5. የሰው ዳግም መወለድ
regeneration_amክርስቶስ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ስለሆነ፣ ሰው አሁን የእግኢአብሔርን ሕይወት ወደ መንፈሱ ውስጥ መቀበል ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ዳግም መወለድ ብሎ ይጠራዋል (1ጴጥ. 1፥3፤ ዮሐ. 3፥3)። ይህንን ሕይወት ለመቀበል፣ ሰው ወደ እግዚአብሔር በንስሐ መመለስ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያስፈልገዋል (ሐዋ. 20፥21፤ 16፥31)።

ዳግመኛ ለመወለድ፣ በቀላሉ በተከፈተና በእውነተኛ ልብ ወደ ጌታ ቅረብና እንዲህ በለው፦

ጌታ ኢየሱስ፣ ኃጢአተኛ ነኝ።
ለእኔ ታስፈልገኛለህ።
ስለ እኔ ስለሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ።
ጌታ ኢየሱስ፣ ይቅር በለኝ።
ከኃጢአቶቼ ሁሉ አንፃኝ።
ከሞት እንደተነሳህ አምናለሁ።
አሁኑኑ እንደ አዳኜና ሕይወቴ እቀበልሃለሁ።
ወደ ውስጤ ግባ! በሕይወትህ ሙላኝ!
ጌታ ኢየሱስ፣ ለሃሳብህ ራሴን ለአንተ እሰጣለሁ።

6. የእግዚአብሔር ሙሉ ማዳን
ዳግም ከመወለድ በኋላ፣ አማኝ መጠመቅ ያስፈልገዋል (ማር. 16፥16)። full-salvation_amከዚህም በኋላ እድሜ ልክ የሚፈጀውን ከአማኙ መንፈስ ወደ ነፍሱ ውስጥ የመሰራጨት ሂደት እግዚአብሔር ይጀምራል (ኤፌ. 3፥17)። ይህ መለወጥ (ሮሜ 12፥2) ተብሎ የሚጠራው ሂደት የሰውን ትብብር ይጠይቃል (ፊልጵ. 2፥12)። አማኙ ፍላጎቶቹ፣ ሃሳቦቹ፣ እና ውሳኔዎቹ ሁሉ ከክርስቶስ ፍላጎቶች፣ ሃሳቦች፣ እና ውሳኔዎች ጋር አንድ እስከሚሆኑ ድረስ ጌታ ወደ ነፍሱ እንዲሰራጭ በመፍቀድ ይተባበራል። በመጨረሻም፣ ክርስቶስ ሲመለስ እግዚአብሔር የአማኙን አካል በሕይወቱ ሙሉ ለሙሉ ይሞላዋል። ይህም መክበር ተብሎ ይጠራል (ፊልጵ. 3፥21)። ስለዚህ፣ በየክፍሎቹ ባዶና የተበላሸ በመሆን ፋንታ፣ ይህ ሰው በእግዚአብሔር ሕይወት ሙሉ ለሙሉ የተሞላ ይሆናል። ይህ የእግዚአብሔር ሙሉ ማዳን ነው! እንዲህ ያለው ሰው እግዚአብሔርን ይገልጣል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ዓላማ ያሟላል!

Article written by

One Response

  1. Senaite Tilahun at | | Reply

    ❤👌👌

Please leave a reply

%d bloggers like this: